ጤና

የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት ማዕከል ግንባታ ተጀመረ

By Yonas Getnet

September 19, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 9፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆነው ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የማገገሚያ ህክምና አገልግሎት ማዕከል ግንባታ ተጀምሯል።

የማዕከሉን መሰረተ ድንጋይ ያስቀመጡት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በወቅቱ እንዳሉት፤ መንግስት ባለፉት ዓመታት ለጤናው ዘርፍ ትኩረት በመስጠት ግብዓት የማሟላት እና መሠረተ ልማት የመዘርጋት ስራ እየሰራ ነው።

ለአዕምሮ ጤና እና ለአካል ድጋፍ አገልግሎት ትኩረት በመስጠት የተጀመሩ ስራዎች ቢኖሩም ይበልጥ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

በተለይም የአዕምሮ እና የአካል ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖች ተደራሽ ለማድረግ እየተከናወነ ያለውን ሥራ ይበልጥ ለማጎልበት መሰል ግንባታዎች ወሳኝ መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

የማዕከሉ ግንባታ መንግስት ለጤናው ዘርፍ የሰጠው ትኩረት ማሳያ እንደሆነ አንስተው፤ የማዕከሉ ግንባታ ሲጠናቀቅ የድጋፍ እና የማገገም አገልግሎትን እንደሚሰጥ አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ አካል ድጋፍ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ታሪኩ ታደሰ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ሲበቃ አዕምሯዊ እና አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች አገልግሎት በመስጠት ቀዳሚው ይሆናል ብለዋል።

ግንባታው 17 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ሲሆን በሦስት ዓመት ውስጥ ተገንብቶ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

በይስማው አደራው

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!