ፋና ስብስብ

የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር ዛሬ ይካሄዳል

By Adimasu Aragawu

September 20, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለሥስት ወራት በብርቱ ፉክክር ሲካሄድ የቆየው የፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ የፍፃሜ ውድድር በዛሬው ዕለት በድምቀት ይካሄዳል።

በውድድሩ ለፍጻሜ የበቁት ጴጥሮስ ማስረሻ፣ እየሩሳሌም አሰፋ፣ እዮቤል ፀጋዬ እና ኤፍሬም ጌታቸው ብርቱ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

የዕለት አቀራረብ ላይ መሰረት በማድረግ በዳኞች እና በተመልካቾች ድምፅ የውድድሩ አሸናፊ የሚለይ ሲሆን፤ በውድድሩ አንድ እንግዳ በክብር ዳኛነት ይገኛል።

በ13ኛው ሳምንት አራት ምርጥ ተወዳዳሪዎችን ይዞ የፍፃሜ ውድድሩን የሚያካሂደው ፋና ላምሮት 5ኛው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ሽልማት የተዘጋጀለት ሲሆን፤ የዋንጫ እና የአዲስ ሙዚቃ ሽልማት ያበረክታል።

ይህን ደማቅ ውድድር በቀጥታ ስርጭት ከቀኑ 6:00 ጀምሮ በፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሁሉም የሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!