የሀገር ውስጥ ዜና

ሕዳሴ ግድብ የማንሰራራት ከፍታ መሸጋገሪያ ማማችን ነው – እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

September 20, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ በስኬት መጠናቀቅ ለጀመርነው የማንሰራራት ከፍታ መሸጋገሪያ ማማችን ነው አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)።

“በሕብረት ችለናል” በሚል መሪ ሐሳብ ግድቡ በስኬት መጠናቀቅን በማስመልከት በክልል ደረጃ የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።

እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚህ በወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በጋራ ያሳኩት አኩሪ ፕሮጀክት ነው።

ኢትዮጵያዊያን በሕብረት፣ በይቻላልና በፅናት ለስኬት ያበቁት የዚህ ትውልድ ጥንካሬ ማሳያ ፕሮጀክት መሆኑን አንስተው÷ በተለይም የለውጡ መንግስት የግድቡ ግንባታ ከነበሩበት ውስብስብ ችግሮች በማውጣት ለውጤት አብቅቶታል ብለዋል።

ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ ስኬት በቀጣይ ለሚከናወኑ ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መሠረት የጣለና ኢትዮጵያ በሀብቷ የመጠቀም መብቷን በተግባር ያረጋገጠችበት መሆኑን ተናግረዋል።

የክልሉ ሕዝብም ለሕዳሴ ግድብ ግንባታ የሚጠበቅበትን ሁሉ ማድረጉን ገልጸው÷ ሕዝቡ ላደረገው ድጋፍም ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሰልፉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!