አዲስ አበባ፣ መስከረም 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ5ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቼልሲ እንዲሁም በመርሲሳይድ ደርቢ ሊቨርፑል ከኤቨርተን የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
ማንቼስተር ዩናይትድ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 1 ሰዓት ከ30 ላይ ኦልድትራፎርድ ይካሄዳል።
የውድድር ዓመቱን በጥሩ ውጤት ያልጀመረው ማንቼስተር ዩናይተድ ካለፉት አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው አንዱን ብቻ ሲሆን÷ አንድ ጊዜ አቻ ሲያጠናቅቅ ሁለቱን ተሸንፏል፡፡
ቼልሲ በበኩሉ ሁለቱን ሲያሸንፍ ሁለቱን በአቻ ውጤት ተላያይቷል።
ቀን 8 ሰዓት ከ30 ሁለቱ የሊቨርፑል ከተማ ክለቦች ሊቨርፑል እና ኤቨርተን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ጨዋታው በአንፊልድሮድ ሲደረግ ሊቨርፑል ያለፉት አራት የሊጉ ጨዋታዎችን በድል የተወጣ ሲሆን÷ ኤቨርተን በበኩሉ ሁለቱን ጨዋታዎች ሲያሸንፍ አንድ ሽንፈት እንዲሁም አንድ ጊዜ በአቻ አጠናቋል፡፡
በሊጉ ሌሎች መርሐ ግብሮች ብራይተን ከቶተንሃም፣ በርንሌይ ከኖቲንግሃም ፎረስት፣ ዌስትሃም ዩናይትድ ከክሪስታል ፓላስ፣ ዎልቭስ ከሊድስ ዩናይትድ ቀን 11 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በተጨማሪም ምሽት 4 ሰዓት ሁለቱ የለንደን ክለቦች ፉልሃም እና ብሬንትፎርድ ይጫወታሉ፡፡
በአቤል ነዋይ