አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአፋር ክልል በጎርፍ ለተፈናቀሉ ሰዎች የሚደረጉ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን የክልሉ የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የክልሉ የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ሀላፊ አቶ መሀመድ ሁሴን እንደገለጹት፤ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በቅርቡ የተከሰተው ድንገተኛ የጎርፍ አደጋ በርካቶችን አፈናቅሏል።