አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋሞ ዞን የ’ዮ ማስቃላ’ በዓል አከባበር አካል የሆነው የጋሞ ብሔረሰብ የባሕል፣ ታሪክና ቋንቋ ሲምፖዚዬም በአርባ ምንጭ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
ሲምፖዚዬሙ”ዱቡሻና ዱቡሻ ወጋ ለዘላቂ ሰላማችን እና ልማታችን” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡
በመርሐ ግብሩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ የባሕልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
ከጋሞ ብሔረሰብ በርካታ ባሕላዊ እሴቶች መካከል ሕግና ደንብ የሚወጣበት፣ የሚሻሻልበት፣ መሃላ የሚፈፀምበት፣ “ጎሜ” የሚያልቅበት እና ዕርቅ የሚወርድበት የተከለለ ሥፍራን የሚያመለክተው ዱቡሻ አንዱ ነው፡፡
“ዱቡሻና ዱቡሻ ወጋ” ባሕሉ እና ትውፊቱ ተጠብቆ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሸጋገር በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑ ተጠቁሟል።
በሲምፖዚዬሙ የዕደጥበብ ሥራ ውጤቶችን፣ የብሔረሰቦችን ባሕላዊ ምግቦችና መጠጦች፣ የባህል አልባሳትና ጌጣጌጦችን እንዲሁም ሌሎች ታሪካዊ ቅርሶችን የያዘው የጋሞ ዞን ኢትኖግራፊክ ሙዚዬም ተመርቆ ለእይታ ክፍት ተደርጓል።
የጋሞ ሕዝብ የሰላም፣ አብሮነትና አንድነት መገለጫ የሆነው የ ‘ዮ ማስቃላ’ በዓል በነገው ዕለት በልዩ ድምቀት ይከበራል።
በማስተዋል አሰፋ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!