የመስቀል በዓል አከባበር ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብክ ሊሆን ይገባል – ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል በዓል የሰላም በዓል በመሆኑ የበዓሉ አከባበር ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብክ ሊሆን ይገባል አሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ።
ቤተክርስቲያኗ የ2018 ዓ.ም የመስቀል በዓል አከባበር ዝግጅትን በተመለከተ መግለጫ ሰጥታለች።
መግለጫውን የሰጡት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ በዕለቱ በሁሉም መንገድ የሚተላለፉ መልዕክቶች ሰላምንና ፍቅርን የሚሰብኩ ሊሆን ይገባል ብለዋል።
በበዓሉ ላይ ኢትዮጵያዊ ባህላችንን የጠበቀ የአለባበስ ሥርዓት መከተል እንደሚገባና ልዩነትን የሚሰብክ አለባበስም ሆነ ምልክት መጠቀም እንደማይገባ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በዚህም በበዓለ መስቀሉ ዕለት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ እና የቤተክርስቲያንን አርማ ብቻ መጠቀም ይገባል ነው ያሉት።
ለክብረበዓሉ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉን ገልጸው÷ ከፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ስለመሆኑም አንስተዋል።
የበዓሉ ተሳታፊዎች የመስቀል በዓልን በመስቀሉ የተደረገልንን በማሰብ እንዲያከብሩም መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በሄኖክ ለሚ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!