አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያንን የዘመናት ቁጭት የመለሰ ነው አሉ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ።
የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ በድሬዳዋ ከተማ ስቴዲየም የድጋፍ እና የደስታ መግለጫ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡
ከንቲባ ከድር በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ የሕዳሴ ግድብ በመላ ኢትዮጵያውያን ትብብር እና አንድነት እውን የሆነ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ብለዋል፡፡
የሕዳሴ ግድብ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር የኢኮኖሚ ነጻነት ማረጋገጥ እንደሚቻል ብርሃን ያሳየ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በፕሮጀክቱ ግንባታ የታየውን የኢትዮጵያውያን ትብብር በቀጣይ በሌሎች ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ መድገም እንደሚገባም አመልክተዋል፡፡
ሕዳሴ ግድብ በሀገር ውስጥ የሃይል ተደራሽነትን ከማሳደግ ባለፈ የቀጣናውን የሃይል ትስስር እንደሚያጠናክርም ተናግረዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡- YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!