አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ ልዑካን ቡድን በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ኒውዮርክ ገብቷል።
የልዑካን ቡድኑ አባላት አሁን ላይም ‘ደህናነት በአብሮነት’ በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ በሚገኘው 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፉ ነው፡፡
ልዑካኑ በጉባዔው ላይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅሞች እንዲሁም የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ ያደርጋሉ፡፡
ከጉባዔው ጎን ለጎንም የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን የውይይት መድረኮች ላይ ኢትዮጵያ የራሷን ብሔራዊ ጥቅሞች ቅድሚያ በመስጠት እንደምትሳተፍ ተመላክቷል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!