የሀገር ውስጥ ዜና

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም ወር ለሚከበሩ በዓላት ዝግጅት ተደርጓል

By Yonas Getnet

September 22, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ10 ብሔረሰቦችን የዘመን መለወጫ በዓላት በጋራ ለማክበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል አለ የክልሉ ባሕልና ቱሪዝም ቢሮ።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ሳሙኤል መንገሻ እንዳሉት ÷ በክልሉ በሚከበሩ የዘመን መለወጫ በዓላት ላይ ከ409 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ቱሪስቶች ይታደማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ባሕላዊ እሴት ያላቸው በዓላቱ ለቱሪዝም ዘርፉ የጎላ አበርክቶ እንዳላቸው ገልጸው ÷ ለአከባበር ሥነ ሥርዓታቸውም በቂ ዝግጅት መደረጉን አመልክተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ የቱሪዝም ሃብቶችን ትርጉም ባለው መልኩ ለመጠቀም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ረገድ የዘንድሮው የዓለም የቱሪዝም ቀን በክልሉ መከበሩ ትልቅ ዕድል መሆኑን ነው ያስረዱት፡፡

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስከረም ወር በሚከበሩ በዓላት የሚታደሙ እንግዶች የቱሪስት መስሕቦችን እንዲጎበኙም ጠይቀዋል፡፡

በተካልኝ ኃይሉ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!