አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋሞ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ “ዮ ማስቃላ” በዓል በአርባምንጭ ከተማ በድምቀት እየተከበረ ነው።
ዮ ማስቃላ በዓል በብሔረሰቡ ዘንድ ዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን ያዘነን የሚያጽናና፣ የተጣላን የሚያስታርቅ፣ የተራራቀን የሚያቀራርብ ልዩ ትርጉም ያለው በዓል ነው።
በበዓሉ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ እና በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌደራልና ክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በተጨማሪም ከተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የተወጣጡ እንግዶች በበዓሉ ላይ ታድመዋል።
በዓሉ በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ነው እየተከበረ የሚገኘው።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!