የሀገር ውስጥ ዜና

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ

By Tibebu Kebede

August 16, 2020

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስን መከላከል የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮችን እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ።

በዩኒቨርሲቲው የምርምርና የማህበረሰበ አቀፍ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር አቢዮት አስረስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በኮሮና ቫይረስ ዙሪያ ያተኮሩ ከ24 በላይ የጥናት ሃሳቦች ቀርበው በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ከወጣው ትኩረት አቅጣጫ ጋር የሚቀራረቡ 18 ጸድቀው በሂደት ላይ ይገኛሉ ብለዋል።