አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላፉት መልዕክት፤ በፊቼ ጨምበላላ የዘመን ቆጠራ እውቀት እና ፍልስፍናው የሚታወቀው የሲዳማ ሕዝብ የሕዳሴ ግድብን መጠናቀቅ ውብ በሆነው የቄጣላ ስርዓቱ በድምቀት አክብሯል ብለዋል።
ሕዳሴ የዓባይን ወንዝ እራት እና መብራት ሆኖ የኢትዮጵያ ልጆችን የልማት ተስፋ እውን ሊያደርግ እንደ አድማስ ዐለት በጽናት እና በትብብር መንፈስ የቆመ የሕዝቦች እውነት እና ታሪክ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዓባይን ከሺህ ዓመታት በኋላ ከሀገሩ ጋር ያስማማው የሕዳሴ ድል የሲዳማ ክልልንም የሀገራዊ የልማት እቅዶች በይቻላል መንፈስ እንዲሰራ ዕድል እንደሚፈጥርለት ገልፀዋል፡፡
ሕዳሴ ግድብ በሀገር ወዝ ተሞሽሮ ጉባ ላይ የቆመ የልማት ሐውልታችን እና መቻላችን የተረጋገጠበት ሕዝባዊ ዐሻራ ነው ብለዋል፡፡