የሀገር ውስጥ ዜና

የማሽቃሮን ዕሴት በማዳበር ለልማትና ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል ይገባል – ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)

By Adimasu Aragawu

September 23, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የማሽቃሮን ዕሴት በማዳበር ለልማትና ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል ይገባል አሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)።

የካፈቾ ብሔር የዘመን መለወጫ “ማሽቃሮ” በዓል ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተገኙት የነገስታት መናገሻ በሆነው “ቦንጌ ሻምበቶ” ተከብሯል።

ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) በበዓሉ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት÷ የማሽቃሮ ዕሴት የሆኑ አብሮነትና አንድነትን በማጠናከር ለልማትና ለሕብረ ብሄራዊ አንድነት ግንባታ ማዋል ይገባል ብለዋል።

የካፈቾ ብሔር ድንቅ የተፈጥሮ ጥበቃ ባህል ባለቤት መሆኑን አንስተው÷ የብሔረሰቡ ድልብ የእውቀትና ጥበብ መገለጫ የሆነውን ማሽቃሮ በመጠበቅ እና በማልማት ለትውልድ ማስተላለፍ እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የካፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እንዳሻው ከበደ በበኩላቸው÷ ማሽቃሮ የአብሮነት፣ አንድነት እና እርቅ መገለጫ መሆኑን አንስተው÷ በዓሉ በዩኔስኮ እንድሚዘገበ እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!