አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አብሮነትን በማጎልበት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ እንደ “ያሆዴ” ያሉ ባሕላዊ እሴቶችን ማጠናከር ይገባል አሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፡፡
የሀዲያ የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” በዓል በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በሆሳዕና ከተማ በድምቀት ተከብሯል፡፡
እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት÷ ኢትዮጵያ የደመቁ ባህሎችና ቋንቋዎች እንዳላትና ከነዚህም የሀዲያ የዘመን መለወጫ “ያሆዴ” አንዱ መሆኑን ተናግረዋል።
“ያሆዴ” ከአሮጌው ወደ አዲሱ ዘመን አብሮነትን በማፅናት በፍቅርና በደስታ የመሸጋገሪያ ወቅት ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አብሮነትን በማጎልበት የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚረዱ እንደ “ያሆዴ” ያሉ ባህላዊ እሴቶችን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!