አዲስ አበባ፣ መስከረም 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ለኢትዮጵያ መድን እግር ኳስ ክለብ የቡድን አባላት የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡
ክለቡ በአጠቃላይ ከ25 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን እንዲያሳካ ላስቻሉት ሁሉም የቡድኑ አባላት ሽልማት ማበርከቱን የክለቡ ፕሬዚዳንት ምንተስኖት ደሳለኝ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡
ሽልማቱ በክለቡ ባለፈው አመት ሲጫወቱ የነበሩ ነገር ግን አሁን ከክለቡ የለቀቁ ተጫዋቾችንም ያካትታልም ነው የተባለው። የክለቡ አሰልጣኝ ገብረመድን ኃይሌ በዚሁ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት፥ ለውጤቱ መገኘት የተጫዋቾቹ ሚና ከፍተኛ ነበር ብለዋል።
ኢትዮጵያ መድን በ2017 ዓ.ም የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዋንጫን በክለቡ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡
በሌዊ በለጠ