አዲስ አበባ፣ መስከረም 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎፋ ዞን ሕዝቦች የዘመን መለወጫ የጎፋ “ጋዜ ማስቃላ” እና የኦይዳ “ዮኦ ማስቃላ” በዓላት በሳውላ ከተማ በድምቀት እየተከበሩ ነው፡፡
በአከባበር ሥነ ሥርዓቱ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፣ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ታድመዋል፡፡
የጎፋ ዞን ሕዝቦች የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ የሆኑት በዓላቱ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነትና የአንድነት ባሕላዊ እሴቶችንና ትውፊቶችን በሚያንጸባርቁ መልኩ ነው እየተከበሩ የሚገኙት፡፡
ዘመናት በተሻገረ አብሮነት የተጋመዱና ባሕላዊ እሴቶቻቸው ተወራርሰው የተሰናሰሉት የጎፋና የኦይዳ ሕዝቦች በየራሳቸው የጊዜ ቀመር የዘመን መለወጫ በዓላት አሏቸው፡፡
የጎፋ “ጋዜ ማስቃላ” እና የኦይዳ “ዮኦ ማስቃላ” የዘመን መለወጫ በዓላትንም በወንድማማችነት እሴቶች አንድነታቸውን አጽንተው በጋራ በታላቅ ድምቀት ያከብራሉ፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!