የሀገር ውስጥ ዜና

በቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት የምርምርና ጥናት ስራዎች ወሳኝ ናቸው

By Adimasu Aragawu

September 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቱሪዝም ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት ጠንካራ የምርምርና ጥናት ስራዎች ወሳኝ ናቸው አሉ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ።

“ቱሪዝም ለዘላቂ ለውጥ” በሚል መሪ ሐሳብ 5ኛው ሀገር አቀፍ የቱሪዝም ዘርፍ ጥናትና ምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ሚኒስትሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ኢትዮጵያ እምቅ ታሪካዊ፣ ባህላዊ እንዲሁም ተፈጥሯዊ ሃብት ያላት ሀገር በመሆኗ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባንን ጥቅም ማረጋገጥ ይገባል።

ጉባኤው በዘርፉ የተገኙ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ያስችላል ያሉት ሚኒስትሯ÷ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት ጠንካራ የምርምርና ጥናት ስራዎች ወሳኝ መሆናቸውን አንስተዋል።

ጉባኤው በዘርፉ ያለውን ጥናትና ምርምር ከማሳደግ ባለፈ እንደሀገር ማግኘት የሚገባን ጥቅም እንድናገኝ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።

በመድረኩ ኢትዮጵያ ያላት እምቅ የቱሪዝም አቅም በተለያዩ የዘርፉ ምሁራንና ተሳታፊዎች ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በዓለምሰገድ አሳዬ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!