ዓለምአቀፋዊ ዜና

በማላዊ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የ85 ዓመቱ ፒተር ሙታሪካ አሸነፉ

By Hailemaryam Tegegn

September 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በማላዊ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የ85 ዓመቱ የሀገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ፒተር ሙታሪካ አሸንፈዋል፡፡

ከፈረንጆቹ 2014 እስከ 2020 ማላዊን የመሩት ፒተር ሙታሪካ በዘንድሮው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ 56 በመቶ ድምጽ በማግኘት ማሸነፋቸውን የሀገሪቱ ምርጫ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በምርጫው 33 በመቶ ድምጽ ማግኘት የቻሉት ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ላዛሩስ ቻክዌራ ለተመራጩ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የአፍሪካ ህብረት ለተመራጩ ፕሬዚዳንት ፒተር ሙታሪካ እንዲሁም ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ በመጠናቀቁ ለማላዊያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፏል፡፡