የሀገር ውስጥ ዜና

በነቀምቴ ከተማ አንዲት እናት 5 ልጆችን በአንድ ጊዜ ተገላገለች

By Adimasu Aragawu

September 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በነቀምቴ ከተማ አንዲት እናት አምስት ልጆችን በአንድ ጊዜ በሰላም ተገላግላለች፡፡

ወ/ሮ አስቴር ተረፈ የነቀምቴ ከተማ ነዋሪ ስትሆን÷ ከአምስት ዓመት በፊት አንዲት ሴት ልጅ ተገላግላ ነበር፡፡

አሁን ላይም በወለጋ ዩኒቨርሲቲ ኮንፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በአንድ ጊዜ አምስት ልጆችን በሰላም ተገላግላለች፡፡

ወ/ሮ አስቴር ሦስት ወንድ ልጆችና ሁለት ሴት ልጆችን በሰላም መገላገሏን የሆስፒታሉ የማሕጸን ሕክምና ስፔሻሊስት ዶ/ር ቢቂላ ለሚ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል፡፡

እናትና የተወለዱት አምስት ሕጻናት በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙም አመልክተዋል፡፡

በመብራቴ ሁንዴ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!