አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊነት በማስጠበቅ የትኛውንም ግዳጅ በአስተማማኝ ብቃት መወጣት የሚችል ጠንካራ ሠራዊት ተገንብቷል አሉ የመከላከያ ሠራዊት ጄነራል መኮንኖች።
የመከላከያ ሠራዊት የሰው ሃብት አመራር ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ክብር፣ አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም በአመራር ልህቀት በአስተማማኝ ደረጃ ጠንካራ ሠራዊት እየተገነባ ነው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የመከላከያ ሠራዊት በትጥቅ የተሟላ፣ አስተማማኝ ቁመና ያለው ጠንካራ የሀገር ዘብ መገንባቱን አመልክተው፤ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ግን የሚያስቡት የተዳከመች ሀገር ማየት እንደነበር ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ጠላቶች የመከላከያ ሠራዊት ግዳጁን በአግባቡ መፈጸም የማይችል እንዲሆን በማለም የጥፋት ግባቸውን ለማሳካት ቅዠት ውስጥ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም በአስተማማኝ መልኩ የሚጠብቅ ጠንካራ ቁመና ላይ የሚገኝ የሀገር ዘብ መገንባቱን ገልጸው፤ ለአብነትም በየጊዜው በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል የሀገራቸውን ሉዓላዊ አንድነት እያስጠበቁ እንደሚገኙ አብራርተዋል።
ሌተናል ጄነራል አጫሉ ሸለመ ለጦር መኮንኖች መስከረም 10 ቀን 2018 ዓ.ም የተሰጠው ሹመት ከዚህ ቀደም ለተመዘገበው ስኬት ብቻ ሳይሆን ተጨማሪ ግዳጅና ተልዕኮ መኖሩን ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
ሹመቱ የሠራዊቱን የማድረግ አቅም በማሳደግ ከብረት የጠነከረ ኃይል የመገንባት አካል ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑንም አስረድተዋል።
የመከላከያ ሠራዊት የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ብርጋዴር ጄነራል ጌትነት አዳነ በበኩላቸው፤ መንግስት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ማስጠበቅ የሚያስችሉ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች መያዙን ገልጸዋል።
መከላከያ ሠራዊት የኢትዮጵያን ጥቅምና ፍላጎት በመፃረር በተቃርኖ የሚንቀሳቀሱ ኃይሎችን አደብ በማስገዛት የተሰጠውን ግዳጅ በብቃት እየተወጣ እንደሚገኝ አስረድተዋል።
ለሠራዊቱ የጦር መኮንኖች የተሰጠው ሹመት በሥነልቦና የበለጠ በመገንባት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማጽናት ቀላል ትርጉም የሚሰጠው አይደለም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት በርካታ የበሬ ወለድ ውዥንብር መረጃዎችን በጽናት በመወጣት በተግባር ተፈትኖ ያለፈ መሆኑን አንስተው÷ በአሁኑ ወቅትም ፀረሰላም ኃይሎችን አደብ በማስገዛት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና ሉዓላዊ አንድነት በማስጠበቅ ለገባለት ቃል ኪዳን ታምኖ እያገለገለ ይገኛል ብለዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!