የሀገር ውስጥ ዜና

በሲዳማ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ

By Hailemaryam Tegegn

September 25, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ የተገነባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ስራ ጀምሯል፡፡

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ እና የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ተመርቆ ክፍት ተደርጓል፡፡

በማዕከሉ 11 የፌዴራል፣ የክልልና የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ተቋማትን ጨምሮ አሁን ላይ 34 አገልግሎቶች እንደሚሰጡ ተገልጿል።