የሀገር ውስጥ ዜና

በባሕርዳር የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻ ተካሄደ

By Yonas Getnet

September 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በባሕርዳር ከተማ የመስቀል ደመራ በዓልን አስመልክቶ የፅዳት ዘመቻ ተካሂዷል።

የፅዳት ዘመቻው በአካባቢ ጥበቃ ጽዳትና ውበት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተካሄደ ነው።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የባሕርዳር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተሻገር አዳሙ እንዳሉት፤ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የ2018 ዓ.ም የመስቀል በዓል በማስመልከት የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ተካሂዷል።

የከተማዋን ፅዳትና ውበት በመጠበቅ ለኑሮ ተስማሚ ለማድረግ የተጀመሩ ስራዎች ህብረተሰቡን በማሳተፍ ተጠናክረው እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!