አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ 253 ቤቶችን ለሀገር ባለውለታዎች እና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች አስተላልፈዋል።
ከንቲባ አዳነች በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እጅግ በመጎሳቆላቸው ፈርሰው የተገቡ 253 ቤቶችን ነው የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው የሀገር ባለውለታዎችና ጧሪ ደጋፊ ለሌላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ያስረከቡት፡፡
በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከተገነቡ 3 ሺህ በላይ ቤቶች ውስጥ 1 ሺህ 924 ቤቶች የቅድሚያ ቅድሚያ ለሚገባቸው ወገኖች መተላለፋቸውን ከንቲባዋ ተናግረዋል፡፡
ቤቶቹ የጸዱ፣ መሰረታዊ ግብዓቶች የተሟሉላቸው፣ ዘመናዊ እና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን የሚፈጥሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የራሳቸው ቅጥር ጊቢ፣ የጋራ መገልገያ፣ የሕጻናት መዝናኛ እና የንግድ ሱቆችን እንዳካተቱ ነው የገለጹት፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!