አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2018 የመስቀል በዓልን በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት ታከብራለች፡፡
ቤተክርስቲያኗ የደመራ በዓል በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ሀገረስብከት በሚገኘው ጽዮን ማርያም ቁምስና በደመቀ ሁኔታ ለማክበር መዘጋጀቷን ገልጻለች፡፡
የቤተክርስቲያኒቱ የጳጳሳት ጉባኤ ጽ/ቤት ለፋና ዲጂታል እንደገለጸው፥ የመስቀል በዓል በነገው ዕለት በልደተ ማርያም ካቶሊክ ካቴድራል በመስዋዕተ ቅዳሴ ይከበራል፡፡
የመስቀል እና የደመራ በዓላቱ ብጹዓን አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓቶች በድምቀት እንደሚከበር ጽ/ቤቱ ጠቁሟል፡፡