አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጋምቤላ ክልል የመስቀል ደመራ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ128 የህግ ታራሚዎች ሙሉ ይቅርታ አድርጓል፡፡
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ወ/ሮ ዓለሚቱ ኡሞድ ባስተላለፉት መልዕክት÷ ታራሚዎቹ በቆይታቸው መታረማቸውን፣ መታነፃቸውን እና መጸጸታቸውን በመገንዝብ በይቅርታ እንዲወጡ ተደርጓል ብለዋል።
ታራሚዎች ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉ መልካም ሥነ ምግባር በመላበስ ለዘላቂ ሰላም እና ልማት የድርሻቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
ህብረተሰቡ ይቅርታ ለተደረገላቸው ታራሚዎች ወገናዊ አቀባበል በማድረግ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተሰማርተው ራሳቸውንና አካባቢያቸውን እንዲለውጡ ድጋፍ ሊያደርግላቸው ይገባል ብለዋል፡፡
የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ አቶ ዶል ኡኮሪ በበኩላቸው÷ የህግ ታራሚዎቹ የይቅርታ አዋጁን መስፈርት አሟልተው የተገኙ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ይቅርታ የተደረገላቸው ታራሚዎች በድርጊታቸው የታረሙ፣ የተጸጸቱና የበደሉትን ህዝብ እና መንግስት ለመካስ ዝግጁ እንደሆኑ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡
በዚህም መሰረት በክልሉ ከሚገኙ አራት ማረሚያ ቤቶች ለ128 የህግ ታራሚዎች ሙሉ ይቅርታ መደረጉን ጠቅሰው፣ ከነዚህም ውስጥ አራቱ ሴቶች መሆናቸውን ቢሮ ኃላፊው ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!