የሀገር ውስጥ ዜና

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለመስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

By Yonas Getnet

September 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ለ2018 ዓ.ም መስቀል በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው፤ የመስቀል በዓል እንደገና የመገለጥና እንደገና የማንሣት በዓል ነው ብለዋል።

መስቀሉ ከ300 ዓመታት በላይ ተቀብሮ የጠፋና የተረሳ፤ ያለቀና የደቀቀ መስሎ እንደ ነበር አንስተው፤ ከዘመናት በኋላ ግን ብርቱ መሪ ሲያገኝ ደመራው ተደምሮ፣ ተራራው ተቆፍሮ እንደገና በመውጣት ተገልጧል ብለዋል።

ይህ ለኢትዮጵያም የሚሠራ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ እንደገና ትነሣለች፣ እንደገና ታበራለች፣ እንደገናም ለዓለም ትገለጣለች ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!