አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመስቀል ደመራ በዓል ኢትዮጵያ በዓለማቀፍ ደረጃ በማይዳሰስ ቅርስነት ካስመዘገበቻቸው መካከል አንዱ ነው፡፡
በዓሉ በመላው ኢትዮጵያ ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተወራረሰ እና ተጠብቆ የቀጠለ ክዋኔን የሚያሳይ የኢትዮጵያ ብዝኃነት እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ማሳያ ነው፡፡
በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበዉም ይህንን ነባር የአከባበር ትውፊቱን ይዞ እንዲቀጥል፣ ከኢትዮጵያ አልፎ የሰው ልጆች ኹሉ የጋራ ቅርስነቱ እንዲጠበቅ ለማስቻል ነው፡፡
ኢትዮጵያውያንም የመስቀል ደመራ በዓልን በየዓመቱ ጥንታዊነቱንና ማኅበራዊ እሴቱን ጠብቀዉ ያከብሩታል፡፡ መንግሥት ልዩ ትኩረት ከሰጣቸዉ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ለኾነው የቱሪዝም ዕድገትም የራሱን ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡
የዘንድሮዉን የመስቀል ደመራ በዓል የምናከብረዉ ደግሞ ኢትዮጵያውያን በጋራ ያሳካነውን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ድልን እያከበርን ባለንበት ወቅት ነው፡፡ ይህም በዓሉን የበለጠ ደማቅ ያደርገዋል፡፡
እንኳን ለመስቀል ደመራ በዓል አደረሳችሁ! የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!