የሀገር ውስጥ ዜና

የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል አደባባይ እየተከበረ ነው

By Yonas Getnet

September 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ በተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶች መከበር ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ክብረ በዓሉም በጸሎት አስጀምረዋል።

በበዓሉ ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች፣ ምእመናን እና ቱሪስቶች ተገኝተዋል።

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!