የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የመስቀል ደመራ በዓል እየተከበረ ነው 

By Mikias Ayele

September 26, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የ2018 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በተለያየ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት እየተከበረ ይገኛል።

በላዛሪስት ገዳም ፂዮን ማርያም ቤተክርስቲያን እየተከበረ በሚገኘው የመስቀል ደመራ በዓል ሥነ ሥርዓት ቅዳሴ፣ መዝሙር፣ ስብከትና ሌሎችም መንፈሳዊ ሥርዓቶች እየቀረቡ ነው።

እንዲሁም የመስቀል ደመራን የተመለከቱ የተለያዩ ሀይማኖታዊ ሥነ ሥርዓቶችም እየተከናወኑ ይገኛል፡፡

በመስቀል ደመራ ሥነ ሥርዓቱ የሀይማኖት አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።

በየሻምበል ምህረት