አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የሰላም ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት፣ ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የጸጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር ለስድስት ቀን ሲያካሂድ የነበረውን ውይይት በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ውይይቱ የህግ ማስከበርና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች የተዳሰሱበት ሲሆን በፌደራል፣ በክልልና በከተማ አስተዳደሮች ባለፈው በጀት ዓመት በጸጥታና ደህንነት ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን አፈጻጸም ጠንካራና ደካማ ጎኖች በጥልቅ ገምግሟል፡፡