አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ6ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሰባት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዕለቱ የመጀመሪያ ጨዋታ ማንቼስተር ዩናይትድ ቀን 8፡30 ከሜዳው ውጭ ብሬንትፎርድን ይገጥማል፡፡
በውድድር ዓመቱ ሁሉንም ጨዋታዎች ማሸነፍ የቻለው የሊጉ መሪ ሊቨርፑል ቀን 11 ሰዓት ላይ ከሜዳው ውጭ ከክሪስታል ፓላስ ጋር ይገናኛል፡፡
በተመሳሳይ ሰዓት ማንቼስተር ሲቲ በርንሌይን እንዲሁም ቼልሲ ብራይተንን በሜዳቸው ያስተናግዳሉ፡፡
ሊድስ ዩናይትድ ከቦርንማውዝ 11 ሰዓት፣ ኖቲንግሃም ፎረስት ከሰንደርላንድ ምሽት 1፡30 እንዲሁም ቶተንሃም ከወልቭስ ምሽት 4 ሰዓት የሚደረጉ ሌሎች የዛሬ ጨዋታዎች ናቸው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook FBC (Fana Broadcasting Corporate S.C.) Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook WMCC TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!