ስፓርት

ኒውካስል ዩናይትድ ከአርሰናል የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

By Yonas Getnet

September 28, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።

በ6ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ዛሬ መድፈኞቹ ምሽት 12፡30 ላይ ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ።

የሊጉ መሪ የሆነው ሊቨርፑል በትናንትናው ዕለት ሽንፈት ማስተናገዱን ተከትሎ አርሰናል በመካከላቸው ያለውን የአምስት ነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ ይገባል።

አርሰናል ከዚህ በፊት በሴንት ጀምስ ፓርክ ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች ምንም ግብ ሳያስቆጥር የተሸነፈ ሲሆን÷ ዛሬም በሚያደርገው ጨዋታ ከባድ ፈተና ይጠብቀዋል።

በአርሰናል በኩል የቡድኑ አምበል ማርቲን ኦዴጋርድ እንዲሁም ቡካዮ ሳካ ለመጫወት ብቁ ሲሆኑ÷ በኒውካስል በኩል የክንፍ መስመር ተጫዋቹ አንቶኒ ጎርደን ከቅጣት መልስ በውድድሩ ይሰለፋል።

በተቃራኒው ፋቢያን ሻር፣ ጃኮብ ራምሴ እና ዮአን ዊሳ በጉዳት ምክኒያት ለኒውካስል የማይሰለፉ ተጨዋቾች ናቸው።

በተመሳሳይ በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ቀደም ብሎ ቀን 10፡00 ላይ አስቶን ቪላ ከፉልሃም ጋር ይጫወታሉ።

በዮናስ ጌትነት

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!