የሀገር ውስጥ ዜና

በአማራ ክልል የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ጀመረ

By Yonas Getnet

September 28, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በማዕከሉ የሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) እና ሌሎች የፌዴራልና ክልል ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ 14 ተቋማትን በውስጡ የያዘ ሲሆን÷ 47 አገልግሎቶችን እንደሚሰጥ በመርሐ ግብሩ ተጠቁሟል።

ማዕከሉ በመንግሥት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚስተዋሉ ቅሬታዎችን በመፍታት ቴክኖሎጂ መር የሆነ ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት በማገዝ እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን እንደሚረዳ ተመላክቷል።

በደሳለኝ ቢራራ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!