ቢዝነስ

የቡና ጥራትን መጠበቅ ለውጭ ምንዛሪ ዕድገት…

By Adimasu Aragawu

September 29, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዲላ የቡና ምርት ጥራት ምርምርና ሰርተፍኬሸን ማዕከልን ሥራ አስጀምሯል።

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ መሪሁን ፍቅሩ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ ለቡና ምርት ጥራት ትኩረት በመስጠት ምርቱን ማሳደግ የአምራቾች ግዴታ መሆን አለበት ብለዋል።

የቡና ጥራትን በመጠበቅ የሀገሪቱን ውጭ ምንዛሪ ማሳደግ እንደሚገባም ጠቁመዋል።

የክልሉ ቡናና ቅመማ ቅመም ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጴጥሮስ ወልደማሪያም በበኩላቸው በክልሉ የቡና ሽፋን 235 ሺህ ሄክታር በላይ መድረሱን አንስተው÷ የማዕከሉ መቋቋም በጥራት ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) የማዕከሉ ግንባታ 17 ሚሊየን ብር የፈጀና ዘመናዊ የቅምሻ ማዕከል መሆኑን ተናግረዋል።

ይርጋጨፌ ቡና በዓለም ላይ ስማችንን ያስጠራ በመሆኑ ይህንን በማስጠበቅ በርካታ ተግባራትን በቡና ዘርፍ መሥራት ይጠበቅብናልም ነው ያሉት።

ባለሥልጣኑ ለማዕከሉ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

በማቱሳላ ማቴዎስ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!