አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሬቻ ዋዜማን በማስመልከት የተዘጋጀው የኢሬቻ ባዛርና ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በዛሬው ዕለት ተከፍቷል፡፡
በባዛርና ኤክስፖው የተለያዩ የባህል አልባሳት፣ ጌጣጌጦች፣ የግብርና እና ሀገር በቀል የኢንዱስትሪ ምርቶች ቀርበዋል።
የባሕል ልውውጥ የሚደረግበትና ወዳጅ ዘመድ በሚገናኝበት ኢሬቻ ባዛርና ኤክስፖ የባህል አልባሳትን ጨምሮ የተለያዩ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚቀርቡም ተመላክቷል፡፡
መርሐ ግብሩ አንድነትን፣ ምስጋና እና ፍቅርን መሰረት በማድረግ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል ትስስር ለማጠናከር ያስችላል፡፡