አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢሬቻ በዓል ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር በማድረግ ለቱሪዝም ፍሰት የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ ይበልጥ ማሳደግ ይገባል አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
የኢሬቻ በዓል እሴቱን ጠብቆ ለማክበር በተካሄዱ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ዙሪያ ከአባገዳዎች እና ሃደ ስንቄዎች ጋር ውይይት ተደርጓል።
ከንቲባዋ በውይይቱ ወቅት እንዳሉት፤ የኢሬቻ በዓል በርካታ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሀገራት ጎብኚዎች የሚሳተፉበት በዓል ነው።
ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ በደመቀና ባማረ መልኩ እንዲከበር በማድረግ ለቱሪዝም ፍሰት የሚያበረክተውን ጉልህ አስተዋጽኦ ይበልጥ ማሳደግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ አባገዳዎች በበኩላቸው፤ ኢሬቻ በአደባባይ የሚከበር የኦሮሞ ህዝብ ለፈጣሪው ምስጋና የሚያቀርብበት የሰላም፣ የእርቅ እና የወንድማማችነት በዓል ነው ብለዋል።
በዓሉ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን ገልጸው፤ ከፍተኛ የባህላዊ አልባሳት እና የሆቴሎች አገልግሎት ግብይት የሚካሄድበት በመሆኑ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሰፊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።
የኮሪደር እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ስራዎች ለአደባባይ በዓላት ምቹ ሁኔታን መፍጠራቸውን ገልጸው፤ በዓሉ በደመቀ መልኩ እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከተማ አስተዳደሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!