የሀገር ውስጥ ዜና

የአፋር ክልል የፀጥታ ኃይልን ለማጠናከር የፌዴራል ፖሊስ ቁርጠኝነት…

By Yonas Getnet

September 29, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአፋር ክልል የሰሜን ምስራቅ ሚሌ ፈጥኖ ደራሽ እና የኮንትሮባንድ ቁጥጥርና ክትትል መምሪያዎች ካምፕ በዛሬው ዕለት ተመርቋል።‎

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ እንዳሉት ÷ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የክልሉን ሰላም ለመጠበቅ በጀግንነት ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

ተቋሙ የክልሉን የፀጥታ ኃይል ለማጠናከር በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን ገልጸው ÷ ላደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል። ‎ ‎የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በበኩላቸው÷ ፌደራል ለግዳጅ በተሰማራባቸው አካባቢዎች የተለያዩ ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት ማከናወን የሚያስችል አቅም ገንብቷል።

ሰራዊቱ ከጀግናው የአፋር ሕዝብ እና ከሌሎች የፀጥታና ደህንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት የኢትዮጵያን ሰላም እና ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እየጠበቀ ይገኛልም ነው ያሉት፡፡

ፌደራል ፖሊስ የሎጂስቲክስ አቅሙን ለማሳደግ ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ እያስረከበ እንደሚገኝ የተናገሩት ደግሞ የሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር እሸቱ ፊጣ ናቸው።

የሚሌ ፈጥኖ ደራሽ መምሪያና የኮንትሮባንድ ቁጥጥር መምሪያ ካምፕ በራስ አቅም እና ወጪ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉንም አመልክተዋል፡፡

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!