አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምሁራን ለሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥሉ የፖሊሲ ግብዓትን በጥናት ማውጣት ላይ ይበልጥ ሊሰሩ ይገባል አሉ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናት ምርምር ተቋም ጋር በመተባበር ያዘጋጁት 22ኛው ዓለም አቀፍ የምርምር ዓውደ ጥናት በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት ÷ የሀገርን ለውጥ ለማስቀጠል እና የሕብረተሰቡን ችግሮች በፍጥነትና በዘላቂነት ለመፍታት ምሁራን የምርምር ሥራዎቻቸውን ሊያጠናክሩ ይገባል።
የምሁራንን የሀገር ግንባታ ሚና ለማሳደግ የምርምር ዓውደ ጥናቶች ወጥና ተከታታይ በሆነ መልኩ ሊካሄዱ እንደሚገባ ጠቁመው ÷ ለሀገር ግንባታ መሰረት የሚጥሉ የፖሊሲ ግብዓትን በጥናት ማውጣት ላይ ምሁራኑ ይበልጥ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በዓለም አቀፍ የምርምር ዓውደ ጥናቱ ላይ የሚቀርቡ የምርምር ውጤቶች ለሀገር እድገት የፖሊሲ ግብዓትነት የሚያገለግሉ ናቸው ብለዋል።
ዓለም አቀፍ የምርምር ዓውደ ጥናቱ ከተመሰረተ 60 ዓመት እንዳስቆጠረና በተለያዩ ሀገራት ሲካሄድ እንደቆየ ያነሱት ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም ዳይሬክተር ዮሀንስ አድገ (ዶ/ር) ናቸው።
ለፖሊሲ አውጪዎች እና ፈጻሚዎች በርካታ ጠቃሚ ግብዓት አስገኝቷል ማለታቸውንም ኢዜአ ነው የዘገበው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!