ጤና

የሥነ ሕዝብ ትሩፋትን በሥነ ተዋልዶ ጤና ለማሳደግ የሚረዳው ፕሮጀክት…

By Melaku Gedif

September 29, 2025

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጤና ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት ልማት ኤጀንሲ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ማሻሻል የሚያስችል የአምስት ዓመት ፕሮጀክት አስጀምሯል፡፡

በኢትዮጵያና አፍሪካ ሀገራት በፍጥነት እያደገ የመጣውን የወጣቶች ቁጥር እና አሳሳቢ የጤና አገልግሎት ፍላጎቶች ለሟሟላት ፕሮግራሙ ወሳኝ ጊዜ ላይ መጀመሩን ተመላክቷል፡፡

ጥራት ያለው የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎትን ተደራሽነት በማረጋገጥ ለተሻሻሉ የጤና ውጤቶች እና ለላቀ የኢኮኖሚ ምርታማነት አስተዋፅኦ እንደሚያበረከትም ተጠቅሷል።

ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ የጤና ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ሲሆን ÷ የወጣቶችን ሥነ ተዋልዶ ጤና በሃገር አቀፍ ደረጃ ያሻሽላል ተብሎ ይጠበቃል፡፡