አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዘንደሮው የዓለም የልብ ቀን በለም አቀፍ ደረጃ ለ27ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ11ኛ ጊዜ “አንድም የልብ ምት አታምልጠን በሚል መሪ ሃሳብ ይከበራል።
የጤና ሚኒስትር ዴዔታ ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በሰጡት መግለጫ ÷ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚከሰቱ ሞቶች ውስጥ አንድ ሶስተኛ የሚሆነው በልብና በደም ስር ሕመሞች አማካኝነት እንደሚከሰት ተናግረዋል፡፡
በኢትዮጵያም በዓመት ከሚሞቱ 100 ሺህ ሰዎች መካከል 220 የሚሆኑት በልብና የደም ሥር ሕመሞች ሳቢያ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ሕክምና ያልተደረገለት ከፍተኛ የደም ግፊት፣ ቁጥጥር ያልተደረገበት የስኳር መጠን፣ በቂ የአካል ብቃት አለማድረግ፣ ሲጋራ ማጤስና አልኮል መጠጥ የልብ ሕመም አጋላጭ መንስኤዎች ናቸው ብለዋል፡፡
የአኗኗር ዘይቤን በመቀየር፣ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግና የአመጋገብ ሥርዓትን በማስተካከል የልብ ሕመምን አስቀድሞ መከላከል እንደሚቻል አመልክተዋል፡፡
ለዚህም ሕብረተሰቡ ምርመራ የማድረግ ባሕሉን ማሳደግ እንዳለበት ነው ሚኒስትር ዴዔታው ያስገነዘቡት፡፡
በሚኒስቴሩ የበሽታ መከላከል መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሕይወት ሰለሞን በበኩላቸው÷ ሕብረተሰቡ በጤና ተቋማትና ሆስፒታሎች የቅድመ ልየታ ምርመራ አገልግሎት እንዲያገኝ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን ሕብረተሰቡ በልብ ሕመም መንስኤና መከላከያ ምገዶች ዙሪያ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ የበኩላቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውንም ሚኒስቴሩ ለፋና ዲጂታል ገልጿል፡፡
በኢትዮጵያ በልብና በደም ሥር ሕመሞች አማካኝነት የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ የልብ ሕሙማን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ እንዳለ ገብሬ ናቸው፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!