አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል በዕቅድ ላይ የተመሰረቱ ተግባራት ይጠናከራሉ አሉ።
ርዕሰ መስተዳድሩ በፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከተመራ ቡድን ጋር ተወያይተዋል።
ውይይቱ በክልላዊ ኢኮኖሚያዊ አካውንት፣ በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት፣ በዲጂታል ልማት እቅድ እንዲሁም በመንግስት የልማት ፕሮጀክቶች አመራርና አስተዳደር አተገባበር ላይ ያተኮረ ነው።
አቶ ኦርዲን በድሪ በውይይቱ ላይ እንዳሉት፤ በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ስራዎች እንዲቀጥሉ እቅድን መሰረት ያደረጉ ተግባራት ይጠናከራሉ።
ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ከለውጡ ወዲህ የመንግስት ፕሮጀክት የማስተዳደር እና የመፈፀም አቅም አድጓል።
ተወዳዳሪ ኢኮኖሚን ለመገንባት እንደሚሰራ ገልጸው፤ ለዚህም በዲጂታል ልማት፣ በክልላዊ ኢኮኖሚ እና በስታትስቲክስ ልማት የተጀመሩ ስራዎችን እንደሚጠናከሩ አረጋግጠዋል።
በክልሎች የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በቅንጅት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በተስፋዬ ኃይሉ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!