አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዩቲዩብ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የቀረበበትን ክስ ተከትሎ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል ተስማማ፡፡
ባለቤትነቱ የጉግል ኩባንያ የሆነው ዩቲዩብ በፈረንጆቹ 2021 ዶናልድ ትራምፕ ስልጣናቸውን ለአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለማስረከብ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተከትሎ በዋሽንግተን ሁከት በተነሳበት ማግስት የዶናልድ ትራምፕን አካውንት ለቀናት ዘግቶ እንደነበር ይታወሳል።
በወቅቱ የተፈጠረውን ሁኔታ ተከትሎ ከዩቲዩብ በተጨማሪ ኤክስ እና ፌስቡክ የፕሬዚዳንቱን አካውንት በጊዜያዊነት ማገዳቸው ይታወቃል።
ይህንን የኩባንያዎቹን ውሳኔ ተከትሎ ‘ፖለቲካዊ መድሎ ተፈፅሞብኛል’ በሚል ወደ ፍርድ ቤት ያመሩት ዶናልድ ትራምፕ ኩባንያዎቹ ላይ የጥፋተኝነት ውሳኔ ማስወሰን ችለዋል።
በዚህም ጥፋቱን አስቀድሞ ያመነው ዩቲዩብ የ24 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ካሳ ለመክፈል መስማማቱ የተገለፀ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ኤክስ እና ፌስቡክ በፍርድ ቤት የሚወሰንባቸውን የገንዘብ ካሳ ለፕሬዚዳንቱ ይከፍላሉ ተብሏል፡፡
ትራምፕ ከዩቲዩብ ከሚያገኙት ካሳ 22 ሚሊየን ዶላሩን በናሽናል ሞል ትረስት ፈንድ አማካኝነት በነጩ ቤተመንግሥት ለሚገነባው አዲስ አዳራሽ ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገብተዋል ነው የተባለው፡፡
ቀሪውን 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ዶላር ደግሞ የአሜሪካ ኮንሰርቫቲቭ ሕብረትን ጨምሮ የዶናልድ ትራምፕን ክስ ለደገፉ ድርጅቶች እና ግለሰቦች በድጋፍ መልክ ለመስጠት ቃል ገብተዋል መባሉን ዋሽንግተን ፖስት እና ቢቢሲ ዘግበዋል፡፡
በሚኪያስ አየለ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!