የሀገር ውስጥ ዜና

አስተዳደሩ በሻሸመኔ ከተማ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመቱ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ

By Tibebu Kebede

August 17, 2020

አዲስ አበባ ፣ ነሃሴ 11 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ ጉዳት ለደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች 1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር የሚገመቱ የተለያዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ እና ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የተደረገ ነው፡፡

ድጋፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፈቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ነጻነት ጉደታ ለሻሸመኔ ከተማ ከንቲባ አቶ ጉታ ሳቾሬ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉ ፍራሽ፣ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የህጻናት አልባሳት እንዲሁም የምግብ መገልገያ ዕቃዎችን ያካተተ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡