አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ የካዛኪስታኑን ክለብ ካይራት አልማቲን 5 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ45 በተደረገው ጨዋታ ፈረንሳዊው አጥቂ ኬሊያን ምባፔ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሲሰራ÷ ቀሪዎቹን ሁለት ግቦች ኤድዋርዶ ካማቪንጋ እና በራሂም ዲያዝ አስቆጥረዋል፡፡
በሌላ ጨዋታ ጣሊያኑ ክለብ አታላንታ የቤልጂየሙን ብሩጅ አስተናግዶ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ሲቀጥሉ÷ ምሽት 4 ሰዓት ቼልሲ ከቤኒፊካ፣ ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ እንዲሁም ቶተንሃም ወደ ኖርዌይ ተጉዞ ከቦዶ ግሊምት ጋር ጨዋታውን ያደርጋል፡፡
የአምናው የፍጻሜ ተፋላሚ ኢንተር ሚላን ከቼክ ሪፐብሊኩ ስላቪያ ፕራግ፣ ባየርን ሙኒክ ከቆጵሮሱ ፓፎስ፣ አትሌቲኮ ማድሪድ ከኢንትራክት ፍራንክፈርት፣ ማርሴ ከአያክስ አምስተርዳም ሌሎች የዛሬ ምሽት ጨዋታዎች ናቸው፡፡