አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል የሚከበርበትን ኢሬቻ ፓርክ የማፅዳት ስራ እየተከናወነ ይገኛል።
ከአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች የተወጣጡ አመራሮች፣ አርቲስቶችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በፅዳት ስራው ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፅዳት አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ገዛኸኝ ደሲሳ እንዳሉት÷ የኢሬቻ ፓርክን የማስዋብና ፅዳቱን የመጠበቅ ስራ በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሲሰራ ቆይቷል።
ዘንድሮ ሆረ ፊንፊኔ ቅዳሜ መስከረም 24፤ እንዲሁም ሆረ ሀርሰዴ በማግስቱ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም ‘ኢሬቻ ለሀገር ማንሠራራት’ በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል።
ከዚህም ባሻገር እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በተለያዩ አካባቢዎች እሴቱን ጠብቆ የሚከበር ይሆናል፡፡
ሰላም፣ እርቅ፣ ፍቅር፣ ወንድማማችነት እና አንድነት የኢሬቻ በዓል ዋና መገለጫዎች ናቸው።
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!