አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2017/18 መኸር ወቅት ከለማው ሰብል 56 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይጠበቃል።
የክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ባበክር ኸሊፋ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት፤ በመኸር ወቅት 1 ነጥብ 6 ሚሊየን ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ 96 በመቶ ማሳካት ተችሏል።
በዚህም 1 ነጥብ 56 ሚሊየን ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች ተሸፍኖ በጥሩ ቁመና ላይ ይገኛል ብለዋል።
በዘር ከተሸፈነው ሰብል ውስጥ በቆሎ እና ማሽላ አብዛኛውን እንደሚይዝ ገልጸው፤ 768 ሺህ ሄክታር መሬት በበቆሎ እና በማሽላ ሰብሎች መሸፈኑን ተናግረዋል።
በክልሉ የቅባት እህሎች በስፋት እንደሚመረቱ ጠቅሰው፤ አኩሪ አተር ብቻ በ122 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ መዘራቱን ገልጸዋል።
በምርት ዘመኑ የመኸር ወቅት ዝናብ ዘግይቶ የገባ ቢሆንም በሐምሌ እና በነሐሴ ወራት በትኩረት በመስራት ክልላዊ ዕቅዱን ለማሳካት ጥረት ተደርጓል ብለዋል።
በረዶ እና ንፋስ ቀላቅሎ በጣለ ዝናብ አማካኝነት የተጎዱ ማሳዎች ላይ ፈጥነው የሚደርሱ ሰብሎች በድጋሚ እንዲዘሩ ተደርጓል ነው ያሉት።
የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት መከናወኑን አስታውሰው፤ በዚህም 131 ሺህ 500 ኩንታል የሰው ሰራሽ እና 10 ሚሊየን ኩንታል የተፈጥሮ አፈር ማዳበሪያ ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል።
እንዲሁም ከ10 ሺህ ኩንታል በላይ የተለያዩ ሰብሎች ምርጥ ዘር መቅረቡን ገልጸው፤ ተገቢው የአረም እና ተባይ መከላከልና ቁጥጥር ተግባር መከናወኑን ገልጸዋል።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!