አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቶ የነበረው የኮድ 2 እና 3 የተሽከርካሪ ሰሌዳ እጥረት ተቀርፎ በሁሉም ቅርንጫፎች አገልግሎት እየተሰጠ ነው አለ የከተማዋ የአሽከርካሪና ተሸከርካሪ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን፡፡
ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው ባለፈው ሳምንት በአንዳንድ ቅርንጫፎች ከህትመት ጋር ተያይዞ ለሁለት ቀናት የኮድ 2 እና 3 የተሽከርካሪ ሰሌዳ እጥረት ተከስቶ ነበር፡፡
ሰሌዳዎቹ ታትመው መግባታቸውንና እጥረቱን መፍታት መቻሉን ገልጾ፥ በሁሉም ቅርንጫፎች አግልግሎቱ እየተሰጠ ነው ብሏል፡፡