አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የሥም እና የአሰራር ለውጥ አደረገ፡፡
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በሰጡት መግለጫ÷ ተቋሙ በምዕራፍ ሁለት ጉዞው በአዲስ አሰራር እና ስያሜ መምጣቱን ተናግረዋል፡፡
በዚህ መሰረትም የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የነበረው የተቋሙ ስያሜ የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በሚል መለወጡን አስረድተዋል፡፡
ከአሰራር ጋር በተገናኘ ዩኒቨርሲቲው ባለፉት ዓመታት የመንግሥት ሠራተኞችን ብቻ ተቀብሎ ሲያስተምር እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
በአዲሱ አሰራር ግን የትምህርት ሚኒስቴርን መስፈርት የሚያሟሉ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን እንዲሁም ከግልና ከመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሩቃንን ተቀብሎ ያስተምራል ነው ያሉት።
ተቋሙ በአመራርና አስተዳደር ሀገሪቱ የምትመራበትን ሪፎርም በማመላከት፣ በፋይናንስ፣ በኢኮኖሚክስ፣ በዲጃታላይዜሽንና ፈጠራ መስኮች ላይ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው እራሱን በማዘመን ተፎካካሪ ተቋም ከመሆንም ባለፈ ሀገራዊ የስልጠና ማዕከል በማቋቋም ብቁ ዜጋ ለማፍራት እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን ሒደት መጀመሩን ጠቁመው ÷ ተቋሙ የሕግ ጉዳዮችን ካጠናቀቀ በኋላ በቅርቡ በአዲሱ ስያሜ ብቻ እንደሚወከልም አስገንዝበዋል፡፡
በአቤል ነዋይ
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!