👉የዩሪያ ማዳበሪያ ፋብሪካ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ከዳንጎቴ ግሩፕ ጋር በመተባበር የሚገነባ ነው።
👉የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካ በጎልደን ኮንኮርድ ግሩፕ የሚገነባ ሲሆን÷ በዛሬው ዕለት መሠረት ድንጋይን ተቀምጦላቸዋል።
👉ዛሬ ለኢትዮጵያዊያን ሁሉ የሚያኮራ ታሪካዊ ሁነት ተፈፅሟል፤ የሁለት አሻጋሪ ፕሮጀክቶች የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠናል።
👉የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ከሂላል የነዳጅ ስፍራ ድፍድፍ ነዳጅ በማውጣት፣ በማጣራትና በማጠራቀም በአመት 3.5 ሚሊየን ቶን የማምረት አቅም አለው።
👉በሌላ በኩልም የማዳበሪያ ፋብሪካው ከካሉብ የጋዝ ስፍራ በማውጣት እና 108 ኪሎሜትር የማጓጓዣ ቱቦ በመጠቀም በዓመት 3 ሚሊየን ቶን አምርቶ ያቀርባል።
👉እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢንዱስትሪ እድገትን ከማሳየት በላይ ናቸው።
👉እድሎቻችንን የመጠቀም፣ ትብብሮችን የማጠናከር እና ሰላምን የማጽናት የጋራ ኃላፊነታችንን የሚያሳዩ ናቸው።
👉ኢትዮጵያዊያን ሁሉ በኅብረት እና በአንድነት ለእድገት መሰባሰባችንን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪ አቀርባለሁ።
👉ይህን ስናደርግ እውነተኛውን የኢትዮጵያዊ ማንነት መንፈስ በሚያከብር መንገድ በዓለም መድረክ የኢትዮጵያን ስፍራ ከፍ እናደርጋለን።
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
YouTube www.youtube.com/@fanamediacorporation Facebook www.facebook.com/fanabroadcasting Telegram t.me/fanatelevision Website www.fanamc.com TikTok www.tiktok.com/@fana_television WhatsApp www.whatsapp.com/channel/0029VbB0dRxG8l59MUkoWR29 Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment Facebook www.facebook.com/wmccwaltamediaandcommunicationcorporate TikTok www.tiktok.com/@fanamc_entertainment Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!